#Human Rights
Target:
H.E Prime Minister Dr. Abyi Ahmed; tamirtsionstudio@gmail.com
Region:
Ethiopia

ቀን ሰኔ 22 2010 / June 29 2018
ለ ኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠቅላይ ሚንስቴር ዶ/ር አብይ አህመድ
አዲስ አበባ
እኛ ስማችን ከዚህ አባሪ ደብዳቤ ጋር የተያያዘው በመላው አለም የምንገንኝ የመልአከ መንክራት መምህር ግርማ ወንድሙ የወንጌል ተማሪዎች እንደ ሚከተለው አቤቱታችንን በታላቅ አክብሮት እናቀርባለን፡፡
በመጀመሪያ በእርሶ አዲስ የመደመር አስተሳሰብ በሀገራችን እያመጡ ያሉትን የሰላም ፣ የፍቅርና የአንድነት ለውጥ እያደነቅኖት የእርሶን የለውጥ ሂደት ለመደገፍና እውቅና ለመስጠት ሰኔ 16 ቀን 2010 ዓ.ም በተሰበሰበው ህዝብ ላይ በደረሰው የቦንብ ፍንዳታ በደረሰው ጉዳት የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እየገለፅን የለውጥ ሂደቱ ወደ ኋላ እንደማይመለስ እየተማመን እስከ መጨረሻው ከጎንዎት መሆናችንን በዚሁ አጋጣሚ ለመግለፅ እንወዳለን።
አቤቱታችንም ስለ መልአከ መንክራት መምህር ግርማ ወንድሙ የወንጀል ክስ ይሆናል።
ለዚህ አቤቱታ መነሻ የሆነን እርሶ ሰኔ 16 ቀን 2010 ዓ.ም ለህዝቡ ባደረጉት ንግግሮች ውስጥ "አንድ ኢትዮጵያዊ ሲጎዳ ፍትህ ሲጓደልበት የወገኔ ፍትህ ተጓድሏል በሉ፤" ባሉን መሠረት የአባታችን የፍትህ ሂደትም ሆን ተብሎ ተቀነባብሮ በምቀኝነት የተሰራ ሴራ ነው ብለን የምንጮህው በመላው አለም ያለን በብዙ ሺህ የምንቆጠር የወንጌል ተማሪዎች ስንሆን ፤ እኝህ አባት በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጪ በመላው አለም በመዞር የወንጌል ትምህርትና የፈውስ አገልግሎት በመስጠት የሚታወቁ ናቸው። ይህ በህዝብ ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነት ማግኘታቸው እና ብዙ ተከታይ ማፍራታቸው በአንዳንዶች የቤተክርስቲያን አባቶች ዘንድ ቅንዓትና የምቀኝነት ስለያዛቸው ከብዙ ዓመት ሙከራ በኋላ አሁን በቀጥታ ከህግ አስከባሪ አካላት ጋር የረቀቀ ትስስር በመፍጠር በተለያዩ ምክንያቶች በመወንጀል ከሰዋቸዋል፡፡
እኝህ አባት በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አመራር እና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክህነት በተቀነባበረ የሀሰት ክስ ተወንጅለው 3 ወር በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ታስረው የወጡ ሲሆን እስከ አሁን ድረስ ከሀገር እንዳይወጡ ታግደዋል።
ክቡር ጠ/ሚ የክሱን ሁኔታ እና ምክንያት እንዲሁም የህግ አካላት እየፈፀሙ ያሉትን የፍትህ መጓተት በቅርበት ቢያውቁት ለወደፊት ለሚያልሟት ኢትዮጵያ ችግሮቿን ለመፍታት አንድ ትልቅ ማሳያ ይሆኖታል ብለን እናስባለን። በጥቂቱ ስለ ክሱ ለመጥቀስ እኝህ አባት ጥቅምት ወር 2008 ዓ.ም ከሀገር ውጭ መንፈሳዊ አገልግሎት አገልግለው ወደ ሀገር ቤት ሲመለሱ የአዲስ አበባ ፖ/ኮ የበላይ ኃላፊዎች በሚመሩት ቡድንና የሬድዮ ፋና ጋዜጠኞችን በተገኙበት የቤተክርስቲአን ባልሰጠቻቸው ፍቃድ በመጠቀም በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጭ የወንጌል አገልግሎት በመስጠታቸው በሚል የወንጀል ክስ ጥቅምት 17 ቀን 2008 ዓ.ም በቁጥጥር ስር አውለዋቸው ያለ አግባብ የመኖሪያ ቤታቸው እንዲ በረበር ተደርጓል። ሬድዮ ፋናም በማግስቱ ጥቅምት 18 ቀን 2008 ዓ.ም የእኝህን አባት ክብርና ዝናን በሚያጎድፍ መልኩ ሰፊ ዘገባ ስራባቸው፡፡
ይህ ወንጀል በኮሚሽን ደረጃ የሚታይ ባይሆንም ግን ሆን ብለው በፖሊስ ም/ኮሚሽነሩ ቀጥታ ትእዛዝና ተሳታፊነት ተከናውኗል። ፍ/ቤቱ የዋስ መብታቸውን እዲጠብቅላቸው ቢወስንም ፤ ከእስር ሳይወጡ በክስ ላይ ክስ እያቀረቡ ከ3 ወር እስር ቤት ስቃይ በኋላ ንብረታቸውና ፓስፖርታቸው ታግዶ ከሀገር እንዳይወጡም ታግደው በውጭ ሆነው እንዲ ከራከሩ ሆነዋል፡፡ ከተከሰሱበት የመጀመሪያዎቹ ሁለቱ ክሶች ፍ/ቤቱ ሳይቀበላቸው ውድቅ ሆነው ቀርተዋል፡፡ 3ኝው 800ሺ ብር የማጭበርበር ክስ ጉዳይ በፍትሃ ቤሐየር ክስ ተመስርቶ የነበረ ቢሆንም ፍ/ቤቱ ውድቅ አድርጎታል፡፡ ይህው 800 ሺ ብር ወስደዋል የሚለው የወንጀል ክስ ክርክር ሲደረግበት ቆይቶ ሚያዚያ ወር 2010 ዓ.ም ተጠናቅቆ ውሳኔ ለሰኔ 15 ቀን 2010 ዓ.ም ስንጠባበቅ በድጋሚ ቀጠሮ ለቀጣይ አመት ለጥቅምት 28 ቀን 2011 ዓ.ም መቀጠሩ የፍ/ቤት አሰራሩን ባናውቅም ከ6 ወር በላይ ለውሳኔ መቀጠሩ ግራ አጋብቶናል፡፡ ቀጣይም ሌላ የሐሰት ክስ ላለመፍጠራቸው መተማመኛም የለንም፡፡ ክቡር ጠ/ሚር የአቤቱታችን ዝርዝር ሁኔታ በዚህች ወረቀት ላይ ተፅፎ የሚያልቅ ስላልሆነ በ2008 ዓ.ም በሀገር ውስጥ ከህዝብ የተመረጠ ኮሚቴ ስለ አለ ኮሚቴውን አነጋግረውልን እውነታውን እንዲያውቁልን ፖሊስም ሆን ብሎ ሰው ለምን እደሚያገላታ ፡ እንዲጠይቁልን በአክብሮት እንጠይቃለን።
ሀገር ቤት ካሉ ኮሚቴዎች ፥
1ኛ አርቲስት ደሳለኝ ሓይሉ
2ኛ ዶ/ር አዘነ በቀለ
3ኛ ዶ/ር ጤናዬ
4ኛ አቶ ተፈራ አባበለው
5ኛ አቶ ጃራ ሁንዴ
እግዚአብሔር ኢትዮጰያንና ህዝቦቿን ይባርክ፡፡

1/ የተከበሩ ጠቅላይ ሚንስቴር ዶ/ር አብይ አህመድ የመልአከ መንክራት መምህር ግርማ ወንድሙ ለ3 አመታት ያህል የሀሰት ክስ የፍርድ መጓተት እልባት ይሰጠው ዘንድ ጉዳዩን ተመልክተው መፍትሄ እና እልባት ይሰጡን ዘንድ በአክብሮትና በትህትና በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን
2/ የመልአከ መንክራት መምህር ግርማ ወንድሙ ከ3 አመታት በላይ የሆነው የቁም እስረኝነት ይብቃ
3/ በአለፉት 3 አመታት ጊዜ ውስጥ ከ28 ጊዜ በላይ ፍርድ ቤት የቀረቡበትና በተለዋጭ ቀጠሮ የተንገላቱበት የፍርድ ሂደት መፍትሄ ይሰጠው ዘንድ እንጠይቃለን
4/ ኢትዩጵያዊያን እና ኢትዩጵያዊ ያልሆኑ ወገኖችን በእግዚአብሔር ፀጋ እንዲያገለግሉ ያለ አግባብ መንገላታታቸው ቀርቶ በነፃነት በሃገር ውስጥም ይሁን በአለም ዙሪያ የመንቀሳቀስ መብታቸው ያለምንም ገደብ እንዲከበርላቸው ስንል በትህትና እንጠይቃለን

The Petition: የተከበሩ ጠቅላይ ሚንስቴር ዶ/ር አብይ አህመድ የመልአከ መንክራት መምህር ግርማ ወንድሙ ለ3 አመታት ያህል የሀሰት ክስ የፍርድ መጓተት እልባት ይሰጠው ዘንድ ጉዳዩን ተመልክተው መፍትሄ እና እልባት ይሰጡን ዘንድ በአክብሮትና በትህትና በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን ! petition to H.E Prime Minister Dr. Abyi Ahmed; tamirtsionstudio@gmail.com was written by Tamirtsion and is in the category Human Rights at GoPetition.