#Justice
Target:
100000
Region:
Ethiopia
Website:
www.facebook.com

አህባሾች ማን ናቸው ???
..................................................................

የሀበሺ (አህባሽ) መንገድ የጀመረው አብደላ አል-ሐረሪ የተባለ ግለሰብ ነበር፡፡ ግለሰቡ ሐረር የተወለደ ሲሆን የሀይለ ስላሴ መንግስት ቀኝ እጅ ነበር፡፡ ከሃይለስላሴ አማች አንደርጌ ጋር ሆኖ ዓሊሞችን ሲያሳስር፣ መብትና እኩልነትን የሚሉትን ሙስሊሞችን ሲያጠቃ እና ሲሰልል ቆየ፡፡እ.ኤ.አ በ1940 (1367 ሂጅራ) ላይ በሐረር የቁርኣን ሂፍዝ ማዕከል መምህራንን አሳስሮ መርከዙን አስዘጋ፡፡ የመርከዙን ዳይሬክተር ሼህ ኢብራሁም ሀሰንን አሳስሮ 23 ዓመታት አስረፈደባቸው፡፡ አብደላ አል-ሐረሪ የፈጠረው ፊትና ‹‹ፊትነተልኩሉብ›› ተብሎ ይታወቃል፡፡ ከዚያም ወደ አዲስ አበባ በመምጣት በሀደሬ ሰፈር ሙስሊሙን ሲያጋጭ ቆይቶ በ1948 ወደ እስራኤል ተጓዘ፡፡ ለዓመት በዚያ ቆይቶ በ1949 ወደ ሶሪያ ገባ፡፡ ከዚያም በ1950 ወደ ሊባኖስ ተጓዘ፡፡ በሊባኖስ ቁርአን በማቅራት ህፃናትን ማሳደን ቀጠለ፡፡ ቀስ እያለ በመቶዎች የሚቆጠሩ ተማሪች አፈራ፡፡ ከአገር ከወጣ በኋላ ከየሁዳዎች ጋር በሚስጢር ይገናኝ ጀመር። ከፍተኛ ገንዘብ ተመድቦለት እ.አ.አ በ1982 የሊባኖስ የርስ በርሱ ጦርነት ጊዜ ድምፁን አጥፍቶ ሀይሉን አጠናከረ፡፡ ከዚያ በ1980ዎች እስራኤል ሊባኖስ ስትወርና ስታጠቃ የሙስሊሞች ጀመዓ ስትወጋ አህባሾችን ግን ተወቻቸው፡፡ ምክንያቱም የርሷ ወዳጅ ናቸውና ነው፡፡ በ1990 አህባሾች በእስራኤል ተረድተው ወደ ፖለቲካ ገቡ፡፡ በ1992 የሊባኖስ ምርጫ ጥቂት ወንበር አሸንፈው ፓርላማ ገቡ፡፡ ቀስ በቀስ የራሳቸውን ሚሊሻ ጦር መለመሉ፡፡ ሙስሊሙን ማበጣበጡን ገፍተው ቀጠሉ፡፡ ከነርሱ ውጭ ያለውን ሁሉ ‹‹ካፊር›› እያሉ መፈረጁ ተያያዙት፡፡ ለመንግስትና ለእስራኤል መረጃ እየሰጡ ሙስሊሙን ማስመታት ጀመሩ፡፡ ራሳቸውን በውሸት ‹‹የሻፊዒ መዝሀብ እንከተላለን›› እያሉ ያስወራሉ፡፡ አህለል ሱንና ነው። አሻዓሪና ማቶረዲ ነን ይላሉ፡፡ ሱፊያም ነን ይላሉ። ሆኖም የሶፊያ ዓሊሞች በሊባኖስ በሌሎች ሀገራትም
መጀመሪያ እውነት ሱፊያ ናቸው ብለው ተሸደውደው ነበር። ሆኖም በሗላ በዝርዝር ሲያውቋቸው አጋልጠው ምላሽ ጻፉባቸው። ሰዉም እንዲያውቃቸውን እና እናዳይከተሏቸው አስጠነቀቁ።እውነታው ግን እነርሱ የእስራኤል ቀኝ እጅ ናቸው፡፡ ቀሰ በቀስ አል-ሀበሺ የሱንና መንገድ እየበከለ ሺዓ፣ ሪፋኢ፣ ሙርጂአ፣ተክፊር፣ሱፊ፣አል-ጀበሪ፣ ቃዲሪያና ጃህሚያ ወዘተ መንገዶችን ቀይጦ(ስፕሪስሪስ) አድርጎ የራሱን አዲስ መንገድ ፈጠረ፡፡ የዓለም ሙስሊሞችን ማክፈር ያዘ፡፡ አብደላ አል-ሐረሪ ‹‹ሳዑዲ እንዴት ከፈረች?›› ብሎ ሁሉ መጽሀፍ ጽፏል፡፡ የነብዩ (ሶ.አ.ወ) አገር መካና መዲና የካፊር አገር ብሎ ጽፏል፡፡ ይህ ብቻ የየሁዳ መሳሪያ መሆኑን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል፡፡ ለመሆኑ አቋማቸው ምንድነው? ቀጥሎ ጥቂቶችን ብቻ እናያለን፡-
1. ከካፊር ጋር ቁማር መጫወት፣ የካፊርን (ክርስቲያን) ጎረቤት መስረቅና ማጭበርበር ይቻላል ብሎ ያስተምራል።ዋናው እንዳይነቃ በድብቅ ማድረግና ዋናው መጠንቀቅ ነው ብሎ ያስተምራል፡፡ (መጽሐፉ ሰሪህ አል-በያን፣ገጽ 133)

2. ሰሀቦችን ይሳደባል፡፡ አንዳንዶቹን ሰሀቦች ካፊር ናቸው የጀሀነም ናቸው ብሎ ጽፏል፡፡ ለምሳሌ ታላቁን የነብዩ (ሶ.ዐ.ወ) ሆሃባ ሙአዊያ ኢብኑ አቢሱፍያን ካፊር የጀሀነም ሲል ገልጿል፡፡ የነብያችን (ሶ.ዐ.ወ) ባለቤት አዒሻን ተሳድቧል፡፡

3. በነጃሳ መስገድ ይፈቀዳል ይላል፡፡(መጽሐፉ ቡግየቱ ጧሊብ፣ገጽ 99-100)

4. ዘካ የለም ይላል፡፡ ዘካ ከእስልምና ማዕዘናት አንዱ ነው፡፡ አህባሾች ግን ሰው ዘካ እንዳያወጣ ከወረቀቱ ብር(ኖት) ላይ ዘካ የለበትም ይላሉ፡፡ ይህ ማለት በባንክም ይሁን በቤትዎ ቢሊዮን ብር እንኳ ካለዎ ዘካ አይስጡ ብሎ ይቀሰቅሳሉ፡፡

5. ሪባ (ወለድ) መውሰድን ያበረታታሉ፡፡ ባንክ ገንዝ አስቀምጠው ባንኩ የካፊሮች(ወይም ስራ አስኪያጁ ካፊር(ክርስቲያን) ከሆነ ጠላታችን ስለሆኑ ወለዱን መውሰድ ይቻላል ብለው ያስተምራሉ።

6. ሴቶቻቸው ሻሽ ብቻ አድርገው ሱሪ ማድረግ ይችላሉ ይላሉ። ጂንስና ፋሽንንም ያበረታታሉ፡፡

7. በሊባኖስ አገር የሙዚቃ ባንድ አላቸው ይህ ባንዳቸው ‹‹James last›› ይባላል፡፡ ዓመታዊ የሙዚቃ ድግስ ያደርጋሉ:: በዛ ላይ ሴቶችና ወንዶች በጋራ ይጨፍራሉ፡፡

8. የአጅነቢ ሴትን ፎቶ፣ ቪዲዮ አልያም በመስታወት ውስጥ ራቁቷን እንኳ ብትሆን በስሜትም ቢሆን ማየት ይቻላል:: ከቁርአንና ሱና ተቃራኒ ሆነው የተከለከለው በዓይን በቀጥታ ማየት ብቻ ነው ብለው ያስተምራሉ፡፡

9. ‹‹ሪፋዒ›› የተሰኘ ጦሪቃን ያስፋፋሉ:: በኢትዮጵያ ጀምረዋል ይህ ጦሪቃ ከሺዓ ጋር የሚያመሳስለው ብዙ እምነት አለው፡፡ የኢትዮጵያ ሙስሊም ግን ሱኒ ነው፡፡

10. እምነት በልብ ነው ባይሰግዱም ኢባዳ ባይሰራም አንዴ አመንኩ ማለት በቂ ነው ብለው ያስተምራሉ:: (መጽሀፍ አ-ደሊል አልቀዊም፣ ገጽ 7)

11. ተከታዮቻቸው በአሜሪካና ካናዳ የቂብላ አቅጣጫ ካልተቀየረ ብለው ረብሻ ፈጥረዋል፡፡ በመጨረሻም ከመስጊድ ሲባረሩ የራሳቸው መስጊድ በተለየ ቂብላ ላይ ሰሩ። አሁን ከሙስሊሙ በተለየ ቂብላ ነው መስጊዳቸው፡፡

12. ድግምትን አይቃወሙም። ራሳቸውም ይፈፅማሉ፡፡ ለሲህር የሚጠቀሙበት ‹‹ሁቡብ አል-አሀብ›› ብለው የሚጠሩት ነገር አላቸው፡፡

13. ቁርኣን የጂብሪል ቃል እንጂ የአላህ ቃል አይደለም ብለዋል። የአላህ ቃል አይፃፍም ይላሉ፡፡

14. የሚገርመው ይህን ሁሉ የጥመት መንገድ እየተከተሉ ሱፊያ ነን፣ ሻፊዒ መዝሀብ ተከታይ ነን ይላሉ፡፡

15. ከነርሱ እምነት ዉጭ ያሉ ዓሊሞችን እንደያስተምሩ ሆን ብለው ያስተጓጉላሉ፣ ይደበድባሉ፣ ያሳስራሉ፣ ያውካሉ፣ በአንድ ወቅት በሊባኖስ ይህ ችግር በስፋት ፈጥረው ‹‹ሸሪዓ መጽሔት›› በቁጥር 574 እትሙ ‹‹ሊባኖስ ጦርነት በመስጂዱ ውስጥ›› በሚል ርዕስ ጽሑፍ አስነበቦ ነበር፡፡

16. ዓመታዊ የሴቶቻቸው የሂጃብ ፋሺን ሾው አላቸው፡፡ በዚያ ላይ ሂጃብ ከሚለብሱት ሴቶች ጋር በጋራ ይጨፍራሉ፡፡

ahbashe dose not represent Ethiopian Muslim we don't want them in Ethiopian mejlis we need to vote our leader

GoPetition respects your privacy.

The ahbashe dose not represent Ethiopian Muslim we don't want them in Ethiopian mejlis we need to vote our leader petition to 100000 was written by ahmed and is in the category Justice at GoPetition.